ልጆቻችሁን፡ አማርኛ ለማስተማር የሚረዷችሁን አስፈላጊ ነገሮች በነጻ ለማግኘት የምትችሉበት "Amharic beginnings" ወደ ተባለዉ ድህረ ገጽ እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ የሚኖሩበት አካባቢ አማርኛ በዋናነትና በሰፊዉ የሚግባቡበት ቋንቋ አይደለምን? የልጆችዎን የአማርኛ ቋንቋ ችሎታ ለማዳበር አንዳንድ ጠቃሚ ስራዎችን ይፈልጋሉን ? መልስዎ አዎ ከሆነ የገዛ ልጆቻችንን አማርኛ ቋንቋ ለማስተማር ስንል እኛዉ እራሳችን አዘጋጅተን የተጠቀምንባቸውን የመማሪያ እቅዶች፣ የመለማመጃ ወረቀቶች ፤ የተለያዩ ሃሳቦችና የተጠቀምንባቸዉን ዘዴዎች በጥቅሉ በአንድነት ተካተዉ የሰፈሩበት ማህደር ዉሰጥ በመግባት ወስደዉ እንዲጠቀሙባቸዉ በመጋበዝ የተቻለንን ልንረዳዎ እንሞክራለን፡፡ በተጨማሪም በልጆቻችንን ድምጽ የተቀረጹ የቃላት መለማመጃዎችን እንዲሁም የልጆቻችንን የመጀመሪያ ቃላትን የቃላት ማስተማሪያ እንዲሆንዎ እንዲገለገሉባቸው እነጋብዞታለን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በየጊዜዉ የምናስፍራቸዉን እርዕሶችን በመጎብኘት ጠቃሚ የሆኑ አጫጭር ትምህርቶች እና ወደፊት ስለሚወጡ መርሐ ግብሮች ለመረዳት ይችላሉ፡፡ ለትናንሽ ና ለወጣት ልጆችዎ እንዲሁም ምናልባትም ለራስዎ አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን እንደሚያገኙበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም በአካባቢዎ ለሚገኙ ጓደኞችዎ፣ ቤተሰቦችዎ እንዲሁም ይሄን ቢያገኙ ይጠቀማሉ ለሚሏቸዉ ሰዎች በሙሉ ወደዚህ ድህረ ገጽ እንዲጠቁሟቸዉ በትህትናና በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡ በዚህም አጋጣሚ ልናሳስበዎት የምንወደዉ እርስዎ እራስዎ አማርኛ ተናጋሪ ከሆኑ ልጆችዎን ዘወትር በአማርኛ ማናገር ዋነኛዉና ቀላሉ የማሰተማርያ መንገድ መሆኑን ተገንዝበዉ እንዲያናግሯቸዉ አደራ እንላለን፡፡ ስለጎበኛችሁን እናመሰግናለን! ማርታ እና ይበቃል |
Welcome to Amharic beginnings! A place for FREE Amharic learning resources for children of all ages! Do you live in a community where Amharic is not the dominant (main) language? Are you looking for resources to further your children’s Amharic language skills? If your answer is "yes", we would like to help you by sharing our "Amharic Immersion" ideas, Amharic reading/writing worksheets, word puzzles, and coloring pages that we created while teaching our children Amharic. Visit our Toolbox for a variety of free printable worksheets. Also visit our Audio Library (prepared with our children's voices) to learn a new word or two or just print and use our Vocabulary Starter Short List. Also visit our blog for everyday topics, quick notes, mini lessons and upcoming projects. We hope you'll find something for your little gals, little guys, and teenagers or even for yourself! Please also consider telling your friends about us and don't forget to check back for more lessons. Most importantly, if you are a native Amharic speaker, we encourage you to SPEAK TO YOUR KIDS IN AMHARIC. It's should be that simple! Thanks for visiting! Martha and Yibekal |
በእኛ ቤት የተመረኮዙ መስራታቸዉ የተመሰከረላቸዉ የተለያዩ ዘዴዎችና ነጥቦች። 1. የቤት ዉስጥ የመነጋገርያ ቋንቋ ሕግ ማውጣትና ሕጉን ሳያቋርጡ ተግባራዊ ማድረግ ልጆች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ በአማርኛ ማነጋገር ቋንቋዉን ያለምንም ችግር በተፈጥሮ እንዲናገሩት ይረዳቸዋል። 2. አማርኛ መናገርን አማርኛ ከማንበብና ከማጻፍ ጋራ አብሮ ማስተማር። 3. ልጆችን ቋንቋ ለማሰተማር ቋንቋዉ ላይ ብቻ ከማተኮር ቀልድና ጨዋታ በማላበስና በማስመስል ማስተማሩ ጥሩ ዉጤት ያስገኛል። የሰዋሰዉ ስህተት ሲፈጠር እዛዉ ላይ ማረምና ማስተካከል በጣም ጠቃሚ፡ ነዉ። 4. ከልጆችዎ ንግግር የሚታዘቧቸዉን አንዳንድ ድክመቶችና ብቃቶች ተመልሰዉ ለማረምና ልጆችዎ የደረሱበትን የእዉቀት ደረጃ ለማወቅ እንዲራዳ ዘወትር ነጥቦች የሚያሰፍሩበት ማሀደር ከአጠገብዎ አይለየዎ። 5. ልጆችዎ (ጉራማይሌ) አማርኛና ሌላ ቋንቋ እየቀላቀሉ አልፎ አልፎ ቢናገሩ ብዙም አይጨነቁ። ለነገሩም እንኳን እነርሱ ይቅርና ትልልቁም ሰው ያደርገዋል። እንዲህ ሲናገሩ ሲሰሙ በትህትና "ምን አልክ?""ምን አልሽ?" ቢሏቸዉ እራሳቸዉ ወድያዉኑ ያስተካክሉታል ወደፊትም ላለመድገም ሲጥሩ ያዩዋቸዋል። 6. ሁል ጊዜ አዳዲሰ ቃላቶችን ይጨምሩ። ልጆቹንም ሲያስተምሯቸዉ ጨዋታ አዘል ዘዴዎችን ቢጠቀሙ ልጆቹ በጨዋታ መልክ በቀላሉ ይረዱታል። 7. የልጆችዎን ሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት አስመልክቶ የትምህርት ቤት አስተማሪዎቻቸውን ማነጋገር ልጆችዎ በቋንቋቸው ከማፈር ይልቅ ኩራትና ድፍረት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። 8. ዘፈን ቋንቋን ያዳብራል በሃልንም ያስተምራል። ይጠቀሙበት። |
Tips and Tricks that have been proven to work and are entirely based on experiences in our household. 1. Make a household language rule and stick to it – From birth, speak to your children in Amharic so speaking it comes naturally to them. 2. Combine learning to speak with learning to write. 3. Never make language an issue (Having fun is very important)– Correct grammatical errors on the spot. You can turn every opportunity into a playful language lesson. 4. Keep a journal nearby. As your children speak, keep a list of skills that need developing and work on them at the appropriate time. 5. Don't worry about your kids mixing words and languages- It is normal when dealing with bi-lingual kids (We do it, don’t we?) It just means that they have more language sources to draw from. In our case, we just say " come again?" and they will switch it right there. 6. Make sure you’re always building on your vocabulary – be creative with vocabulary games so your children can have fun picking a lesson or two. 7. Talk to your children's teachers. They can be a valuable support system in making your children feel appreciated and proud about their bilingual abilities rather than be ashamed of it. 8. Music is a great cultural and linguistic tool, use it! |