እኛ በትውልድ ኢትዮጵያዊ አማርኛ ተናጋሪ የሆን የሁለት የሚደነቁ ወንድ ልጆች ወላጆች ነን። ለዚህ ድህረ ገጽ መሰረቱና መነሻ ምክንያቱ እኒሁ ልጆቻችን ናቸዉ፡፡ እኛም ብንሆን ልጆቻችንን አማርኛ መናገር ማንበብና ማጻፍ ለማሰተማር ገና ከበፊት ጀምሮ ጠንካራ ፍላጎት ስለነበረን እነሱን ማስተማሩ ትልቅ ደስታና እርካታ ስጥቶናል። ይሄዉ ዛሬ በልጅነት አቅማቸዉ በጣም የሚያኮሩ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ሆነዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ይህንንም ድህረ ገጽ ከእንኛ ቤተሰብ ለመላው ማህበረሰብ እንዲረዳ በሚል ሃሳብ ያዘጋጀነው ሲሆን ያዋቀርነዉም በልጆቻችን ሙሉ ተሳትፎ እና ትብብር ነዉ፡፡
ከሐገር እርቆ በባእድ ሐገር ባህልና ቋንቋ ዉስጥ ተዘፍቆ እየተኖረ ልጆችን አማርኛ ተናጋሪ አድርጎ ለማሳደግ ብዙ ጥረትንና ድካምን ይጠይቃል፡፡ ሆኖም ግን ድካሙና ጥረቱ ዉጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ በእኛ አመለካከት ዘለቄታ ያለዉ ዘዴ ነዉ ብለን የምናምነዉ ከቤታችን ጀምሮ አቅማችን እስከፈቀደዉ ድረስ አካባቢያችንን የአማርኛ መማርያና ማስተማርያ ቦታ ማድረግ ነዉ፡፡ በጥቅሉ ልጆቹ የሚሰሙት የሚያዩትና የሚናገሩት ሁሉ አማርኛ እንዲሆን በማድረግ አማርኛ ቋንቋ ዉስጥ እንዲዘፈቁ ማድረግ ነዉ፡፡ ህጻናት በተፈጥሮ በልጅነት ጊዜአችው ብዙ ቋንቋ የማወቅ ችሎታ አላቸዉ ስለሆነም አማርኛ መናገር እየቻሉ ሌላ ቋንቋ መናገር የሚቀናቸው ከሆነ አይጨነቁ ፤ ጥረትዎና ድካምዎ ከንቱ ሆነ ብለዉ ተስፋ ሳይቆርጡ የጀመሩትን ሳይሰለቹ በጽናት በመቀጠል የሚጠብቁት ዉጤት ላይ ለመድረስ ይቻላል፡፡ ዉጤቱም ሁለት ቋንቋ በመናገር ሁለት ጊዜ ደስታና ሳቅን ማግኘት ይሆናል ! ! ! Tips and Tricks አርእስቱን ይመልከቱ ፡፡ ምኞታችንና ጥረታችን ሁላችሁም ወላጆች ቤታችሁን የአማርኛ መማርያ ቦታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ልጆቻችሁ ኢትዮጵያዊ ባህልና ወጉን ጨምሮ የሚያዉቁበትና ብሎም የሚኮሩበት ቦታ እንድታደርጉት ነዉ፡፡ ይህም በመሆኑ ኑሮዎ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ለመጭዉ ትዉልድ አማርኛ ቋንቋን ለማሰተላለፍ ወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ፥ አጎቶች፣ አክስቶችና መላዉ ቤተሰብ በሙሉ ከእኛ ጋር አብራችሁ እንድትሰለፉ በትህትና እንጋብዛለን። ልጆቻችንን አማርኛ እናናግራችው ። ማርታ እና ይበቃል |
We are native Amharic speaking parents of two amazing boys! Our children have been the inspiration behind this website. Teaching them how to speak, read and write Amharic has been our passion and our joy! They have now become Amharic speaking Ethiopians in their own rights! We are so proud of them! This entire website was created as a family volunteer project with our children’s full participation.
When raising children outside of Ethiopia, parents have to work relentlessly to provide that Amharic learning space. Our approach has been Total Amharic Immersion. To us, that means always speaking in Amharic to our children and surrounding them with a culturally rich environment which sets the perfect platform for Amharic language learning. Children have a natural ability to learn multiple languages in early childhood years. So don’t worry if your child shows a propensity to speak another language in the midst of Amharic conversations. Just continue to be consistent, spend quality time and maintain, maintain and yes maintain! You’ll find that your efforts don’t just go unnoticed. See Tips and Tricks. What are the perks of having a bilingual household? Double the language is double the fun! Our vision is to help and motivate every parent to make their household a place of total immersion, not only of the Amharic language, but also of Ethiopian cultural heritage. Therefore, if you live outside of Ethiopia, in the new season bestowing upon you, we ask you parents, aunts, uncles etc. to join with us on a campaign to pass on the gift of Amharic speaking to the next generation. Let’s begin with speaking Amharic to our children! Martha and Yibekal |